News

የየመን ልዑካን ቡድን የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ም/ቤትን ጐበኘ ዓርብ ሚያዝያ 3 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም የየመን ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ አማካሪዎች፣ የተ

ለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከሲቪክ ማህበራትና ከሴቶችና ወጣቶች የተውጣጡ የልዑካን ቡድን የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ጉብኝት አድርጓል፡፡ የልዑካን ቡድኑን በምክር ቤቱ አዳራሽ ተቀብለው ያነጋገሩት የተከበሩ አቶ ካሣ ተክለብርሃን የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ሲሆኑ ስለኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ሥርዓት አወቃቀር ስለህገ-መንግስት እና ስለብዝሃነት ማብራሪያ በመስጠት ልምድ አካፍለዋል፡፡ በአገራችን ከ2ዐ ዓመታት በፊት የነበሩት ጨቋኝና አምባገነን...የሴኔቶች፣ የሹራ እና የአፍሪካና የዓረቡ ዓለም አቻ ምክር ቤቶች ማህበር ማጠናከር የቀጠናዎቹን ሁለንተናዊ ትስስር በይበልጥ እንደሚያጐለብተው ተገለፀ፡፡

  ከመጋቢት 27-28/2006 ዓ.ም አገራችን 8ኛውን የሴኔቶች፣ የሹራዎችና የአፍሪካና የዓረቡ አቻ ምክር ቤቶች ማህበር መደበኛ ጉባኤንና የማህበህሩን 1ዐኛ የምሥረታ በዓልን በመዲናችን አዲስ አበባ በሚገኘው በአዲሱ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ አስተናግዳለች፡፡ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡ አቶ ኃይለማርያም በንግግራቸው አፍሪካውያን አረቦች ወይም አረብ ያልሆኑ እንደሁም በመካከለኛ...የመንግሥታት ግንኙነት ከማጠናከር አኳያ የሕግ ወይም የፖሊሲ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልግ ተነገረ

  የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ከፎረም ኦፍ ፌዴሬሽንስ ጋር በመተባበር የመንግሥታት ግንኙነት ማዕቀፍ ዝግጅት ግብአት ማሰባሰቢያ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ በራስ አምባ ሆቴል ከመጋቢት 18-19/2006 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ አውደ ጥናቱን በንግግር የከፈቱት የተከበሩ አቶ ካሣ ተክለብርሃን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ናቸው፡፡ መንግሥታችን ለኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔሰቦችና ህዝቦች ድርብ ኃላፊነቶች እንዳሉት የገለፁት አፈጉባኤ ድህነትንና ኋላቀርነትን በመፋለም ፈጣን የልማት...በምክር ቤቱ ላይብራሪ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ መፅሐፍትና ቃለጉባኤዎች በህትመት ገፅ (Publication page) ላይ ይገኛሉ፡፡

   የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት ጽ/ቤት ሠራተኞች ማርች 8 የሴቶች ቀንን አከበሩ

  ረቡዕ መጋቢት 3/2ዐዐ6 ዓ.ም የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት ጽ/ቤት ሠራተኞች ማርች 8 የሴቶች ቀንን በምክር ቤቱ አዳራሽ “የሥርዓተ ፆታ እኩልነት የልማት እቅዶቻችንና የህዳሤያችን መሠረት ነው፡፡” በሚል መሪ ቃል አክብረው ውለዋል፡፡ የበዓሉን አከባበር ሥነ ሥርዓተ በንግግር የከፈቱት የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ ናቸው፡፡ ወ/ሮ ሽታዬ በዓሉን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት ማርች 8 የሴቶች ቀን መከበር ከተጀመረ በዓለም ለ1ዐ3ኛ ጊዜ ሲሆን...Showing 1 - 5 of 73 results.
Items per Page
Page of 15
Chat
Minimize Maximize
Chat is temporarily unavailable.