ብዙም አንድም ሆነን የመለስ ራዕይ ለህገመንግስታችን ለህዳሴያችን !

Inter-Pariamentary unioun

 

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች
ዴሞክራሲያዊ አንድነት ማሳያ ሐውልት ነው!
የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች
ወሳኝ ተሳትፎ እውን ይሆናል!
በአባይ ልማት የተባበሩት ክንዶቻችን በሌሎች የልማት ሥራዎቻችንም ላይ በመድገም
ድህነትና ኋላቀርነትን እናስወግዳለን!
በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ርብርብ የኢትዮጵያ ሕዳሴ እውን ይሆናል!
እኛ ወጣቶች የሀገራችንን ሕዳሴ እውን ለማድረግ ተግተን እንሰራለን!
ሕገ መንግሥታችንና የፌዴራል ሥርዓቱ የሕዳሴያችን መሠረት ነው!
የፌዴራል ሥርዓታችን የአብሮነታችንና የአንድነታችን መሠረት ነው!
ሕገ መንግሥታችን የአንድነታችን፣ የሰላማችንና የነጻነታችን መገለጫ ነው!
ልዩነታችን ውበታችንና ጥንካሬያችን ነው!
በጥረታችን ድህነት ተረት ይሆናል! የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ተግባራዊ
በማድረግ የኢትዮጵያ ሕዳሴ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ እናደርሳለን!
የበለጸገችና የዳበረች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ!

Nation nationality song prepared by House of Federation of FDRE

More Video

.

Number of online user(s) : 1

1610321 : times visited.

 9ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ህዳር 29 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ሰፊ ዝግጅት በመደረግ ላይ ይገኛል፡

 
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን/የህገ መንግስታችን ቀን/ በሀገራችን ረጅም የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፋች የሆነው የመጀመሪያው ፌዴራላዊና ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስታችን የፀደቀበት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የብሔራዊ ማንነት ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ዘላቂ ዋስትና ያገኘበትና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ግንባታ አስተማማኝ የማዕዘን ድንጋይ የተጣለበት የታላቅ ክንውን መታሰቢያ በዓል በመሆኑ ታሪካዊነቱ እጅግ ልዩ ያደርገዋል፡፡

ህገ መንግስታችን ፀድቆ ሥራ ላይ ከዋለ ጊዜ ጀምሮ ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ለህዝቦቿ አስተማማኝ ሰላምና አንድነት የፈጠረ፤ ትክክለኛ የዕድገት አቅጣጫ ይዘን በአዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንድንጓዝ ያደረገን የቃልኪዳን ማሰሪያ ሰነድ ነው፡፡ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እስር ቤት ሆና የነበረችው ሀገራችን ያለፉት ስርዓቶች የፈጠሩትን የተዛባ አመለካከት እና ግንኙነት በማረም ዛሬ የህዝቦች መብት የተረጋገጠበት የዕድገትና የልማት ብሩህ ተስፋ የሰነቀች የእኩልነት፣ የመቻቻልና የመከባበር የፍትህ ሀገር ለመሆን በቅታለች፡፡
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነት፣ ታሪክና ቅርስና ባህል በአደባባይ ደምቆ የሀገር ኩራትና ድምቀት መሆን ችለዋል፡፡ መቻቻል፣ መከባበር እኩልነትና መፈቃቀድን ምሰሶ ያደረገው አንድነታችን ስር እየሰደደ መተማመንና መተሳሰብ በመፍጠር ለሀገራችን ህዳሴና መልካም ገጽታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡
የተለያየ እምነትነቶችና ሃይማኖቶች የሚከተሉ የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በመግባባትና በመረዳዳት መንፈስ አብሮ በመኖር የጋራ ሀገራቸው የሆነችውን አዲሲቷን ኢትዮጵያ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ በጋራ በመረባረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ታሪካዊ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ የጋራ እሴቶቻችን ለሀገራችን ተጨማሪ ክብርና ሞገስ ከማላበስ አልፈው ለልማታችን የማይናቅ ድርሻ በማበርከት ላይ ይገኛሉ፡፡
ልዩነትን እንደ ውበት አንድነትን እንደ ጥንካሬ በመቀበል በህገ መንግስታችን የደመቀው አንድነታችን ይበልጥ እየተጠናከረና እያበበ ለህዳሴያችን ስኬት የማይተካ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ ህገ መንግስታችን ሀገራችንን ከጥፋት በመታደግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከድህነትና ኋላቀርነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ምቹ ሁኔታዎችን የፈጠረ ነው፡፡ ይህንኑ የህገ መንግስታችን አላማ ለማሳካት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዘው በመረባረብ ላይ ይገኛሉ፡፡
9ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔሰቦችና ሕዝቦች በዓል “በህገ መንግስታችን የደመቀ ኢትዮጵያዊነታችን ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል ዓመቱን በመሉ በመላው ሀገራችን የሰላም፣ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሥራዎቻችንን አጠናክረን በመቀጠል የምናከብር ይሆናል፡፡ ይህን በዓል ልዩ ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ የሆነው ህገ መንግስታችን ፀድቆ ስራ ላይ ከዋለ ጊዜ ጀምሮ 2ዐ የሰላም፣ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዓመታትን ያሰለፈና እስከአሁን የተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶችን ይበልጥ በማጠናከር የኢትዮጵያን ህዳሴ በአስተማማኝ ደረጃ ለመድረስ ዳግም ቃል የምንገባበት ዓመት ነው፡፡ በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሚገኝበት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚከበር በመሆኑ ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ልዩ ትርጉም አለው፡፡ በሌላ በኩል ህገመንግስታችንን በማክበርና በማስከበር በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን ምርጫ ፍፁም ነፃ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በማድረግ ሀገራችንን ወደተሻለ የዴሞክራሲ ሂደት የምናደርስበትን መልካም አጋጣሚ ይፈጥርልናል፡፡
የበዓሉ አዘጋጅ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስትና ህዝብ በዓሉ በሰላም፣ በልማትና በዴሞክራሲ እሴቶች ታጅቦ እንዲከበር ለማድረግና የክልሉን መልካም ገጽታ ለሀገራችንና ለውጭ ዓለማት ለማስተዋወቅ ይህ ህብረብሔራዊ፣  ሀገራዊ ውበትና አንድነት በአንድ መድረክ የሚታይበት በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማዘጋጀትና እንግዶቹን ለመቀበል ከወዲሁ ዝግጅቱን በማቀላጠፍ ላይ ይገኛል፡፡ የበዓሉ አስተባባሪ የኢፌዴሪ የፌዴሬሸን ም/ቤት በዓሉን ምክንያት በማድረግ መላው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና በአጠቃላይ ለሀገራችን የህዳሴ ጉዞ የሚያደርጉትን ድጋፍ በሁሉም መስክ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
 

 
 
“በህገ መንግስታችን የደመቀ ኢትዮጵየዊነታችን ለህዳሴያችን!”

 


 

 
 

 

 

 

News News
Minimize Maximize

የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ፎቶዎችን በህትመት (publication) ገፅ ላይ ይመልከቱ፡፡ መስከረም 2007 ዓ.ም

       የ ኢ . ፌ . ዴ . ሪ የፌደሬሽን ም / ቤት አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ ካሣ ተክለብርሃን በውጭ ጉዳይ ሚ / ር ዴኤታ /H.E Yves Rossier/ የሚመራውን የሱዊዘርላንድ ልዑካን ቡድን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡  አፈጉባዔው ለልዑ ካን ቡድኑ ኢትዮጵያ በሕዝቦች ነፃ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የፌዴራሊዝም ሥርዓት በመከተል ...  የአፈሪካና የዓረቡ ዓለም አቻ ምክርቤቶች ማህበር በጆርዳን ኦማን ስብሰባው በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ የማህበሩ አባላት አገራት በኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ የግጭት መንሴኤዎችና መፍትሔዎቻቸው እንዲሁም በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ሲወያዩ ውለዋል፡፡ በዛሬው ውሎው የተከበሩ አቶ ካሳ ተክለ ብርሀን የኢፊዲሪ ፌዴሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባኤና የማህበሩ ሊቀ መንበር በመክፈቻ ...የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት ለመላው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንኳን ለ2ዐዐ7ዓ.ምበሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገል

ፃል፡፡ ም/ቤቱ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የትግል ውጤቱ የሆነውና ሀገራችንን ከጥፋትና ከብተና በመታደግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከድህነትና ኋላቀርነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመድረስ ምቹ ሁኔታዎችን የፈጠረ ህገ መንግስታችን እንዲከበር፤መቻቻል፣ እኩልነትና መፈቃቀድን ምሰሶ ያደረገው አንድነታችን ስር እንዲሰድ መተማመንና መተሳሰብ በመፍጠር ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ህዳሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ   ይገኛል፡፡ ...ሕገ መግስታችንን ማከበርና ማስከበር የሕልውና ጉዳይ እንጂ የምርጫ ጉዳይ አይደለም

    በሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ነፃ ፍላጎት ላይ ያልተመሰረተ፣ የዜጎች ይሁንታ የሌለው ስርዓት ለአስከፊ ጦርነትና ድህነት እንደሚዳርግ ከሌላ ሀገር ሰምተን ሳይሆን ከራሳችን የቅርብ ጊዜ ታሪክ መረዳት ይቻላል፡፡ ያለፉት ሥርዓቶች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማዳፈን ሀገራችንን በከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነትና ድህነት እንድትዳረግ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ሥርዓቱም በሀገራችን ጥሎት ያለፈው ጠባሳ ምንጊዜም በታሪክ ሲዘከር ይኖራል፡፡ ያ...October 23, 2014
S M T W T F S
282930 1 2 3 4
5 6 7 8 9 10 11
12 13 14 15 16 17 18
19 20 21 22 23 24 25
26 27 28 29 30 31 1