Back

ሕገመንግስቱ ለሴቶች ያጎናፀፋቸው የእኩልነት መብት

ሕገመንግስቱ ለሴቶች ያጎናፀፋቸው የእኩልነት መብት እንዲረጋገጥና ከፌዴራል ስርዓቱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ
************************************************************
 በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ላይ የተሳተፉት የሁሉም ክልሎች አፈ ጉባዔዎች፤ ከተፎካካር የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ፤ የሲቨክ ማህበራት እና ባለድርሻ አካላት ሲሆኑ በመድረኩ ላይ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ በአስተላለፉት መልዕክት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግስቱ የበላይነት እንዲረጋገጥና ሕገ መንግስታዊ ስርዓታችን እንዲዳብር፣ በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አገራዊ አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር እንዲሁም የፌዴራል ስርዓታችን ጤናማና ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ ኃላፊነት የተሰጠው ሕገ መንግስታዊ ተቋም መሆኑን በመግለጽ የሴቶች ሕገ መንግስታዊ የፖለቲካ ተሳትፎ ለፌዴራላዊ ዲሞክራሲዊ ስርዓታችን መጎልበትና ቅቡልነት የጎላ ሚና አለው አሉ። እንዲሁም እኩልነት ስንል የሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከወንዶች በእኩልነትና በፍትሓዊነት መሳተፍንም የምጨምር ሲሆን ከዚህ አንፃር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ መንግስቱና የፌዴራል ስርዓቱ የበላይ ጠባቂ ተቋም በመሆኑ የሴቶች ውጤታማ የፖለቲካ ተሳትፎ በሚፈለገው ደረጃ እንድረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የመስራት ኃላፊነት አለበት ሲሉ ገልፀዋል ።
የዳበረና ውጤታማ የዲሞክራሲ ስርዓት መገለጫዎች መካከል የሴቶች እኩል የፖለቲካ ተሳትፎ ማረጋገጥ አንዱና ዋንኛው ስሆን በአገራችንም የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ማደግ እውነተኛና አካታች የዲሞክራሲ ባህል እንዲዳብር ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ በአገራችን ከለውጡ ወዲህ በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ዙሪያ መልካም ለውጦች ታይቷል፡፡ በተለይም በፖለቲካ ሪፎርሙ በርካታ ሴቶች ወደ አመራርነት በመምጣቸውና የአገራችን የፖለቲካ ምህዳር በመስፋቱ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እያደገ ይገኛል።ስለሆነም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እድገት ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው መስራት ይኖርባቸዋል ስሉ የተከበሩ አፈ ጉባዔው የገለጹት ሲሆን አሁን የሚታዩ ውስንነቶችን በማረም በ6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫ የሴቶች ሕገመንግስታዊ የመምረጥና የመመረጥ መብት በተሻለ መልኩ እንዲረጋገጥ ማስቻል ተቀዳሚ ተግባር መሆን አለበት ስሉ ገልፀዋል ።
በመጨረሻም በዛሬው መድረክ በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ዙሪያ ያሉ ተግዳሮቶችና መፍትሔቻቸው ላይ በመወያየት የጋራ መግባባት እንድንፈጥር እንዲሁም 6ተኛው አገራዊ ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች በተሻለ መልኩ ሴት እጩዎች በብዛት የሚቀርቡበትና በፌዴራልም ሆነ በክልሎች የተሻለ ብዛትና ጥራት ያላቸው ሴት አባላት የምናይበት እንዲሆን ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርሻችሁን ለማበርከት ተገቢውን ዝግጅት እንድታደርጉ በማለት በአጽንዖት አሳስበዋል ። ለመድረክ ተሳታፊዎች በሀገራችን የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ የሚገለጽ ጥናታዊ ፁሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተሄደ ይገኛል ።

ጥር /2013ዓ.ም
አዳማ